ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መንግስት በልማት ስም በተያያዘው የማፍረስ እና ዜጎችን የማፈናቀል ዘመቻ ከኢኮኖሚ ባሻገር ያለውን አሉታዊ ማህበራዊ አንድምታ በግሩም ሁኔታ አብራርተዋል። በፓለቲካ አንጻር የሚወሰድ እርምጃ ( ልማት ይባል ምን ይባል) የሚያስከትለው ማህበራዊ መመሰቃቀል አለ። ሃገር ማለት ህዝብ ማለት ከሆነ ፕሮፌሰሩ እንደጠቆሙት የሕዝቡን ማህበራዊ ትስስር እየበጠሱት በሄዱ ቁጥር ሃገር የማፍረሱ ጉዳይ እውን አየሆነ ይሄዳል። ይሄ የጥፋት ስራ ግን የተጠቀለለው በልማት ስም ነው። የተቃዋሚውም ወገን ሃገር ለማዳን በእርግጥ ሁነኛ ስራ አንዲሰራ ከተፈለገ ብዙ መሰራት ያለበት በማህበራዊ አንጻር ነው። ቤት የፈረሰባቸው ፣የተፈናቀሉ ሰዎች ከገቡበት ሃዘን እኩል (ያውም ባይበልጥ) የሚያሳዝን ነገር ቢኖር ወገኖች በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሲወድቁ ሌላው ዜጋ አንደ ኢትዮጵያዊ ቁጭት አና ቁጣ አለማሳየቱ ነው። ያ ደሞ የሚያሳየው በማህበራዊ አስተሳሰባችን ላይ የደረሰውን ውድመት ነው። ማህበራዊ አስተሳሰባችንን ብቻ ሳይሆን እምነታችንንም አንዳጣን የሚያመላክት ነው። አንዲህ ያለ ዜጋ ይዞ የፓለቲካ ለውጥ ተስፋ መሰነቅ ሆነ መጠበቅ ነው ችግሩ አንግዲህ። አስካሁን የምናየው “የሰብአዊ መብት” አና በሌሎች መሰል ጉዳዮች አንጻር የሚደረገው ‘አክቲቪዝም’ የረባ ለውጥ ያላመጣበት አንደኛው ምክንያት ይሄ ይመስለኛል። ማህበራዊ ሁኔታ ትኩረት ይሰጠው። ሁነኛ ግብዐት ነው። እየፈራረሰ ያለውን ማህበራዊ እሴት አና ማህበራዊ አስተሳሰብ ማዳንም ሃገር ማዳን ነው።