Thursday, June 6, 2024
HomeEthiopian Newsአደንዛዢ ማህበራዊ አስተሳሰቦች በነገሡበት የለውጥ ሃሳብ መዝራት ትርጉም አይኖረውም

አደንዛዢ ማህበራዊ አስተሳሰቦች በነገሡበት የለውጥ ሃሳብ መዝራት ትርጉም አይኖረውም

ኢትዮጵያውስጥ ለለውጥ ያለው ተነሳሽነት ለውጥ በሚያስፈልግበት ደረጃ የጠለቀ አይደለም የሚሉ አስተያየቶችን አልፎ አልፎ አሰማለሁ።ሊያስማማ ይችላል። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከኑሮው ጀምሮ እስከ አምነቱ ድረስ የተዘረፈበት ሁኔታ አለ።  ስለዝርፊያው ትርጉም ያለው ተቃውሞ ( በተለይ ከምርጫ 97 ወደዚህ) እንዳላሰማ ይታወቃል። የዜግነት መብቱ አና የሃገር ባለቤትነቱ (ባላገርነቱ) ተረስቶ የኑሮ እና የደህንነት ዋስትናው ስልጣን ላይ ያለውን ወገን በመደገፍ አና ስልጣን ላይ ባለው ወገን በጎ አድራጎት ላይ የተመሰረተ አንዲመስል ሁሉ ተደርጎአል።  አሱም ምንም አልተባለም። ጭራሽ የሚጨበጨብለት የሚደነቅ ሁሉ ሃሳብ አየመሰለ ነው። ሃገርን የሚለውጠው ባለራዕይ ትውልድና ሕዝብ ሆኖ ሳለ ግለሰብ (ያውም የሃገር ፍቅር ያለነበረው)  አንደ ራዕይ ፣አንደ ሃገር አና ህዝብ እየተመለከ ነው። ጉዳዮ ከደነዘዘ ማህበራዊ አስተሳሰብ የሚመጣም ነው። 


የድንዝዝነቱ መጠን የሚለካባቸው ሌሎች ብዙ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል። አሁን ባለው አኳኋን ምናልባት ኢትዮጵያ የማን ናት ብሎ መጠይቅ የአብዮት ጥያቄ ሊመስል ሁሉ ይችላል። አንዳልሞተ ሰው መለስ ዜናዊ በዚህ ገብቶ መለስ በዚህ ወጥቶ አየተባለ የሞኝ  ተረት ሲተረትለት የሚዋለው ነገር  ድንዝዝነቱን ከመለካት ባሻገር ስለሚተረክለትም ትውልድ ስለተራኪውም ባህሪ አና ዓላማም የሚለው ነገር ይኖራል። የበሬ ካራጁ አይነት ግንኙነት የነገሰ ይመስላል። እንደበሬ ሳር አያሳዮ ወደ ገደል ሲወስዱት  ከማንም በላይ ችግሩ ያለው ካለተፈጥሮው የበሬ ባህሪ የተላበሰው ክፍል ላይ ነው—ከበሬም አኮ የሚዋጋም አለ። ግራ አጋብቶአል የዚህ ትውልድ ነገር።
 
አንዲህ ያለውን በጉልበት አና በሌሎች ዘዴዎች የተፈጠረ የደነዘዘ አተሳሰብ የበለጠ ያጠቃው አረጋውያንን አና አቅመ ደካሞችን አይደለም። አዎ የችግሩን አሳሳቢነት ይበልጥ የሚያጎላው አንዲህ ያለውን ሃሳብ አዝሎ አየኖረ ያለው ደሞ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ የለውጥ ሃይል ነው የሚባለው የህብረተስብ ክፍል ነው -ወጣቱ። የገባቸው ጥቂቶችን ፣የሚችሉትን አየሞከሩ ያሉትን አብሬ መውቀሴ አንዳልሆነ መጠቆም እፈልጋለሁ።የሚችሉትን ያህል አየሞከሩ ያሉ የፖላቲካ መሪዎችንም -ሃገር ቤት ያሉትን ማለቴ ነው- አይመለከትም። ስለደነዘዘው ነው የማወራው። አዉቆ የተኛም ካለ -አውቆ ስለተኛውም ነው የማወራው። 

 
አንቆቅልሹን ለመፍታት ሁነኛ ጥረት አየተደረገ አይመስለኝም። የሚለፉት አየለፉ  ቢያንስ ለለውጥ ትርጉም ያለው አንኳን ዝግጁነት የማይስተዋልበት ምክንያት -ምናልባት ዓለት ላይ አንደተዘራው አይነት ነገር ቢሆን ነው። በማህበራዊ አስተሳሰብ ደረጃ ብዙ የተመሰቃቅለ ጉዳይ አለ። ለለውጥ የሚሆን ማህበራዊ ስብዕና ሳይኖር ለውጥ መጠበቅ ብልህነት አይደለም። ለውጥ አልመጣም ብሎ ማማረም አንዲሁ ትክክል አይደለም።  ደጋግሜ አንደምለው በተነዛባቸው ፕሮፓጋንዳ ምክንያት አንደዋዛ አና አንዳልባሌ ነገር የጣልናቸው ኢትዮጵያዊ ማህበራዊ አስተሳሰቦች አሉ። አነሱን አናንሳቸው አና  እስቲ በነዛ በኩል ይሞከር። ራሱን አየሳተ ያለው ትውልድ- የደነዘዘው ትውልድ መጀምሪያ ራሱን ይግዛ። አደንዛዥ ማህበራዊ አስተሳሰቦች በነገሱበት የለውጥ ሃሳብ መዝራት ትርጉም የለውም። ፍሬም አይኖረውም። አደንዛዦቹ ማህበራዊ አስተሳሰቦች ወይንም ወደዚያ የሚወስዱ አስተሳሰቦች ይለዮ። ይዘመትባቸው። የመነጋገሪያ ርዕስም ይሁኑ።   

http://www.youtube.com/user/dbirku?feature=mhee
advertisment

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here