ጓደኛየ ጋር ስለ ሀውልት ጉዳይ ተነሳና –የአባ ጳውሎስን ሃውልት አነሳሁብት። “አሱ አንኳን ትክክለኛ ቦታ ነው የተተከለው። ቦሌ የሙሰኞች አና የሌባ መንደር ነው። “የቦሌ ስብዕና ነበራቸው ማለቱ ነው። የሲሳይ ንጉሱ “ረቂቅ አሻራ ” ትዝ አለኝ !
ምን ለማለት ነው ? ከረባት ለሚለብሱ ሌባዎች አክብሮት የሚቸር ትውልድ አና (ምሁራንም ጭምር ) ተፈጥሮአል ለማለት ነው። አንዲህ ያለውን ጉዳይ አየረሱ ለውጥ መጠበቅ —ሰማይን ማረስ ይሻላል። ሌቦችን የሚያከብር ስብዕና ከአስመሳይነትም የከፋ ችግር የተጠናወተው ነው። የመስረቅ አዝማሚያ ነው። ሌባ አንዴት አንድርጎ ነው ታዲያ ሃገሩን የሚለውጠው ? አንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች ጭራሽ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑበት ማህበረሰብ የሚያፈራውስ ትውልድ ምን አይነት ነው ?
ለለውጥ የሚያስፈልገው ስብዕና የአቡነ ጴጥሮስ ( ስለ ሃይማኖታዊ እምነታቸው አይደለም ያወራሁት – ማውራት ካለብኝ ግን አሁንም ይሄው ከላይ ያልኩት ጓደኛየ የአቡነ ጴጥሮስ ጽናት ይለያል — የመጽሃፍ ቅዱሱ ጴጥሮስ አኮ ክርስቶስን ክዶታል አለኝ። ) አይነት ስብዕና ነው። ለቆሙበት ላመኑበት ነገር ዝንፍ ሳይሉ ማለፍ። ህይወት ማለት ይሄ ነው። አንደሳቸው ማድረግ ቢቀር ደሞ ቢያንስ ከረባት ለብሰው ስርቆት ለሚያጧጡፉ ሌቦች ባይጨበጨብላቸው ምን አለበት ? የሚያጨበጭበው አኮ ከሰረቀው እኩል የሞተ ስብዕና ተሸክሞአል ማለት ነው።
http://www.youtube.com/user/dbirku?feature=mhee