Thursday, June 6, 2024
HomeEthiopian VideoViral VideosEskindir Nega: "He's a journalist, not a terrorist"

Eskindir Nega: “He’s a journalist, not a terrorist”

ፓለቲከኛ ይሁን የፖለቲከኛው ወይ የፖለቲከኞች ደጋፊ ልዮነት በሚንጸባረቅበት እና ፖለቲካዊ ባህሪ ሊይዝ በሚችል ጉዳይ የፖለቲካ መነጸር ቢያጠልቅ ወይ ቢያጠልቁ፤ ጉዳዮን በትግል መንፈስ ቢያዮት የሚገርም ነገር የለውም።

ነገር ግን ፈጽሞ በፖለቲካ በትግል መንፈስ መታየት የሌለባቸው ጉዳዮች አሉ። ከታች ባለው ቪዲዮ ላይ የእስክንድር ባለቤት ስለ ልጁ ናፍቆት ተናገረ ያለችው ነገር ልጂ ለሌለው ሰው እንኳን እንባን የሚያስመጣ ነገር ነው። ገዢም ሆነ የገዢው ወገን ደጋፊ የሆነ ሁሉ ነገሩን ወደ ራሱ እያዞረ ቢያየው ጥሩ ነበር። ሰብአዊነት ማለት ከእውቀት የሚመነጭ ነገር አይደለም። በተፈጥሮ የሚገኝ ሰው አውሬ ላለመሆኑ ማረጋገጫ ነው።

ሲሆን የፖለቲካ ትግል ራሱ ከፓለቲካ ትግልነት ባለፈ ወደማይታረቅ ጠላትነት ስሜት የሚወስድበት ሁኔታ የሚያበቃበት ንቃተ ህሊና ላይ ቢደረስ እና የፖለቲካ ትግል ለሃገር እድገት እና የህዝብ ጥቅም (በሁለንተናዊ ገጽታው) የሚደረግ ገንቢ መስተጋብር ተደርጎ ቢታይ አብዛኛው ለወያኔ የገደል አፋፍ መስሎ የታየው ነገር እንዴት ቀላል እና በፍጹም ወደ ትምክህት እና አጥፍቶ የመጥፋት መንፈስ የሚጎትት ነገር እንደሌለ ራሳቸው ታምሰው ሃገር እያመሱ ላሉት የወያኔ ፊታውራሪዎች ሊረዱት ይችሉ ነበር።

እርስ በርሳችን እንደ አንድ ሃገር ሳይሆን የተለያየ ቋንቋ እንደሚናገር የተለያዮ ሃገር ሰዎች የምንተያይበትን በጎሳ ምህዋር ላይ የሚሽከረከር ስርአት መፍጠሩ ሳያንስ፤ በሰላማዊ መንገድ አዲስ አበባ ላይ ለመብት የሚታገሉ ዜጎችን እያነቁ እስር ቤት መወርወር! መሪዎቹ ስለተሸበሩ በሰላም ሃገር ሽብር ያለ እየመሰላቸው ያልተሸበሩ ሰዎችን ለማሸበር እየሞከሩ፤ እንደገና ዞሮ አሸባሪዎች ናቸው ብሎ መክሰስ በእውነት ትርጉም የሚሰጥ ነገር ነው?

የእስክንድር ልጂ የአባቱን ናፍቆት ለመወጣት በዚህ የልጂነት እድሜው እስር ቤት መዋል ነበረበት?! ለመሆኑ ወያኔ እስክንድርንም ሆነ አንዱዓለምን በማሰሩ የሰላማዊ ሰልፍ ስጋት ቀረለት? ምንድን ነው ያተረፈው? የህግ የበላይነት ማለት ሰላማዊ ዜጋን እስር ቤት እየወረወሩ በቤተሰቡ ላይ ጭምር ሰቆቃ ማድረስ ነው? ምን ዓይነት ድንቁርና ነው?

advertisment

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here