Thursday, June 6, 2024
HomeEthiopian VideoViral VideosGelawa-Ethiopian Music

Gelawa-Ethiopian Music

Gelawa-Ethiopian Music

ቆየት ያለ የፍቅር ዘፈን ቢሆንም ትንሽ ዘመኑን እንዲመስል ተደርጎ እንደገና ተሰርቶ እንኳን ለዛው እንዳለ ነው:: ከቅላጼው መሳጭነት በላይ ፤ ስለሁለት ፍቅረኛሞች የፍቅር ትስስር የሚተርከው ማህበራዊ አንደምታው ሳይዛነፍ ፤ ማህበራዊ ፋይዳውም ሳይዛነፍ ስለሆነ ውበት ጨምሮለታል። ከፍቅረኛሞቹ የፍቅር ትስስር በተጨማሪ ልጂቱ ከአባቷ ጋር ያላት ትስስር ፤ ልጁም ከልጂቷ አባት ጋር ያለው ትስስር ቁልጭ ብሎ ይታያል። በነበሩበት ሁኔታ በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ማህበራዊ ሃላፊነት እና የሚጠበቅባቸው ግብረገብነትም ተንጸባርቋል። ከማህበረሰቡ ጋር የተጣሉ እና ማህበራዊ “ነጻነት” ፍለጋ ማህበራዊ አመጽ ላይ ያሉ ጥንዶች አይመስሉም ። “ኦርጋኒክ” ሊባል የሚችል አይነት እና ብዙ ያልተበረዘ (original) ግንኙነት!ሙዚቃውን የጻፈው ብዙውን ምስጋና ሊወስድ ይገባል። ከማህበረሰቡ ጋር ችግር የሌለበት እና እንዲያውም ጥሩ ትስስር ያለው አይነት ይመስላል።

“ጀነቲካሊ ሞዲፋይድ” ማህበራዊ ሃሳብ በማራገብ ማህበረሰባዊ ካንሰር እየተከሉ ፤ እጂግ ትልቅ ስራ የሰሩ የሚመስላቸው (የሚሞካሹም) አንዳንዴ ቆም ብለው ማህበረሰባችን ከሌላ ማህበረሰብ ብዙ ሳይገለበጥበት የራሱ የሆነው ማህበራዊ አስተሳሰብ እና ግንኙነት ለእድገት መሰረት ሊሆን እንደሚችልም፤ በራሱም መንገድ ማደግ እንደሚችል (በተለይ በማህበራዊ ግንኙነት ጉዳይ) ማሰብ ቢቻል ጥሩ ነበር።

advertisment

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here