Home Blogs ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የሚጋልባቸው የፖለቲካ ፈረሶች

ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ የሚጋልባቸው የፖለቲካ ፈረሶች

0
Photo Credit: ECADF
Photo Credit: ECADF

ማርች 30,2013 (borkena)ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ካደረሰው ጥፋት የማይተናንስ (ያውም ባይበልጥ) ውድመት ያደረሱት እና እያደረሱ ያሉት ወያኔ የሚጋልባቸው ፈረሶቹ ናችው። በሰሞኑ ጉባዔያቸው በሚቆጣጠሩት ሜዲያ ብዙ የደሰኮሩበት የ”ልማት” ዕቅድ አብዛኛው ቅዠት እንደሆነ አምነዋል።

በጥቂት አስርት ዓመታት ‘የኢንዱስትሪ ኢኮኖሚ እንመሰርታለን’ የሚለው ከቅዠቶታቸው አንደኛው ነበር። እንደማይሳካም ማመን ደረጃ ላይ ደርሰዋል። እንደሚገባኝ ባላቸው ነባራዊ ሁኔታ መጀመሪያም ጉዳዮ የሚደረስበት እና ሊሰራ የማይችል እንደሆነ ሳይገባቸው ቀርቶ አይደለም። በግብርናው አንጻር ሊያራምዱ ያሰቡትን የጥፋት ፕሮግራም መሸፈኛ ግርግር መፍጠሪያ ዲስኩር መሆኑ ነበር።

ገበሬው ምርታማ ያልሆነ ፣ ቤተሰቡን መመገብ የማያስችለው በጣም አነስተኛ የመሬት ይዞታ እንዳለው እየታወቀ ፣ምርታማ የሆነ ያልታረሰ መሬትን ለኢትዮጵያውያን ገበሬዎች በማከፋፈል እና ሌሎች ምርታማነትን የሚጨምሩ ፓሊሲዎችን እንደመከተል በአውሮፓ ያሉትን ትናንሽ ሃገራት የሚያካክል ለም መሬት ባልባሌ ዋጋ ለባዕዳን ባለገንዘቦች ተሸጠ፤ በምንም መልኩ የምግብ ዋስትናን እንደማያረጋግጥ እየታወቀ።

ባለራዕይ እየተባለ በሚሞካሸው መለስ ዜናዊ ኢንዲህ ዓይነት ርምጃ የተወሰደው በዋነኛነት እረፍት ይነሳቸው የነበረ የሃይል ሚዛን የበላይነት ጥያቄ ለረዢም ጊዜ አስጠብቆ ለመቆየት ከተወሰዱ ርምጃዎች አንዱ ነው ባይ ነኝ። ያጣ የነጣ፣ የሃገር ባለቤትነት ስሜቱ የተዘረፈ በገቢር ተኮሳምኖ በባርነት የሚኖር ለህወሓት እና ለደጋፊዎቹ የፓለቲካ ስጋት[ለነሱ] የማይሆን ዜጋ ለመፍጠር። እንደዚህ አይነት መሰሪ ትውልድ እና ሃገር የሚግደል ፓሊስ አስፈጻሚ የነበሩት ግን የሕዋሓቶቹ መለስ ዜናዊ እና ጓደኞቹ ይጋልቧቸው የነበሩ የፖለቲካ ፈረሶች ናቸው። ይሄንን ሰፋፊ መሬት ፈርሞ የሸጠው ፈረስ በሰሞኑ ጉባዔ ላይ ስለምርት ማሳደግ ጉዳይ እንዲስ ሲል ተናገረ :-

“መሬት በማስፋት፣የሚታረስ መሬት በመጨመር ምርት ማሳደግ ካነስተኛ አርሶ አደሩ አኳያ ከሞላ ጎደል እየተዘጋ ያለ አማራጭ ወደ መሆን እየመጣ ነው። …እስካሁን እድገቱን ከማረጋገጥ አኳያ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የተሻሉ የሆኑት ትላንት ይነሳ እንደነበረው በአማካይ በሃገር ድረጃ ከ25% አይበልጡም[ወደላይ ሰቀለው]። ከ75 % የሚሆነውን አርሶ አደር ባልደረስንበት ሁኔታ በጂቲፒ የተቀመተ የ40 እና የ50 ሚሊየን ኩንታል ዕድገት ማረጋገጥ አይቻልም። ስለዚህ በዚህ መስክ ለውጥ እናምጣ ካልን ከነዚህ 25% አርሶ አደሮች ወጥተን ወደ 75% ማዕቀፍ መድረስ ይኖርብናል።”

በሚከተለው የኢቲቪ ቪዲዮ ክሊፕ ከ12ኛው ደቂቃ ጀምሮ የሚናገረውን ተከታተሉ…

የሚታረስ መሬት በመጨመር ምርት ማሳደግ የሚቻልበትን ሁኔታ የዘጋው ማን ነው? እንዴትስ ነው የተዘጋው? እንኳን የሚታረስ መሬት የመጨመር ሃሳብ ሊኖር፤ ሕወሓት የተከተለው የጎሳ ፓለቲካ የፈለገውን ያህል ሊፈነዳ የሚችል ቅራኔ እንዳልፈጠረ ግንዛቤ ሲወስዱ ፤ ቅራኔ የማነሳሻ ሌሎች መንገዶች በመከተል በተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል ሰፍረው የመሬት ይዞታ የነበራቸውን ዜጎች እንደ እንግሊዞቹ “በሃገሩ በሬ” በሚል ብሂል ያደረሰውን ነገር እየሰማን ነው። ለሕዋሓት ሃገር የጎጥ መንደር ነው::

በሌላ አንጻር ግን ቅራኔ በሚፈጥርባቸው አካባቢዎች ሕወሓት በብልጣብልጥነት በራሱ ለራሱ ዓላማ የተያያዛቸው እስከጋብቻ የሚደርሱ ማህበራዊ ማለሳለስ እና ትስስር እየፈጠረ እንዳለ የሚጠቁሙ ሁኔታዎች አሉ። በአንድ በኩል በህዝቦች መካከል ቅራኔ ይፈጥራል፤ በሌላ በኩል ደሞ ለበላይነት ህልም /ቅዠት ይጠቅመኛል ብሎ የሚያስበውን የማህበራዊ ፓሊሲ በብልጠት እያካሄደ ነው። ፈረሶቹ ግን አሁንም ፉሩሽካቸውን እየወሰዱ ይጋለባሉ።




__
Join the conversation. Like borkena on Facebook and get Ethiopian News updates regularly. As well, you may get Ethiopia News by following us on twitter @zborkena

NO COMMENTS

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Exit mobile version